Sunday, February 16, 2014

#አስቴር_አወቀ
#ምነው_እግር_አወጣህ

ምነው እግር አወጣህ እንዴት ፈረደብኝ
ያም አንተን ያም አንተን አየሁት በዛብኝ ወዴት ነው መዋያህ ፈራሁኝ እንጃልኝ
አይን በዝቶብሃል ሽሽግ በልልኝ
አይን በዝቶብሃል ሽሽግ በልልኝ
ፍቅር ከረባት አርገሃል
ፍቅር ብለው አወሩልኝ
ፍቅር ካንገቱ አያስንቅም
ፍቅር አውልቀው በሉልኝ
ፍቅር የብርጌጥ አሰራህ
ፍቅር ይሉሃል መንደሩ
ፍቅር ይልቅ ያንተ ገላ
ፍቅር አይሆንም ወይ ጥሩ
ከእግር እስከ ራስህ እንዳሳየሀቸው አይንህን ጥርስህን ግድ የለም በላቸው ልየው ያሉ እንደሆን በለመደ አይናቸው ልብህን አደራ የሷ ነው በላቸው
ፍቅር አይን አይከለከል
ፍቅር ያየሰው ይመኛል
ፍቅር የኔ መሆንህን
ፍቅር ማን ይረዳልኛል
ፍቅር እዛም እዛም አትበል
ፍቅር ፍራት አደረብኝ
ፍቅር ልብህን መርምረው
ፍቅር እንዳያገኙብኝ
ምነው እግር አወጣህ እንዴት ፈረደብኝ
ያም አንተን ያም አንተን አየሁት በዛብኝ ወዴት ነው መዋያህ ፈራሁኝ እንጃልኝ
አይን በዝቶብሃል ሽሽግ በልልኝ
አይን በዝቶብሃል ሽሽግ በልልኝ
ፍቅር ከግር እስከራስህ
ፍቅር እንዳሳየሃቸው
ፍቅር አይንህን ጥርስህን
ፍቅር ግድ የለም በላቸው
ፍቅር ልየው ያሉ እንደሆን
ፍቅር በለመደ አይናቸው
ፍቅር ልብህን አደራ
ፍቅር የሷ ነው በላቸው
ፍቅር ልብህን አደራ
ፍቅር የሷ ነው በላቸው

No comments:

Post a Comment